በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ4ኛ ዙር ከፊታችን ሰኞ ከታህሳስ 12/4/2013 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይፋ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ደሙ በዛሬዉ እለት በሰጡት መግለጫ እንዳሳወቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከሉ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራዉን በከተማዉ ለማስጀመር በተቀመጠዉ ውሳኔ መሰረት ቀደም ሲል ህዳር 16 የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቸ በክለሳ ትምህርት ውስጥ እንዳልፉ ፣ ህዳር 28 በግል ትምህርት ቤቶች ከ1 ክፍል ጀምሮ እና በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ በሶስት ዙሮች መጀመሩን ገልጸዉ ከፊታችን ሰኞ ከታህሳስ 12/4/2013 ዓ/ም ጀምሮ በ4ኛ ዙር ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎች በግል ትምህርት ቤቶች የቅድመ መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ – 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መሆናቸዉን ሀላፊዉ አሳውቀዋል፡፡
ሀላፊዉ በመግለጫቸዉ አክለዉም ህጻናት ተማሪዎችን ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማሩ ስራ እያመጣን በመሆኑ የተዘጋጀዉን የኮቪድ ፕሮቶኮልን በአግባቡ መተግበር እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ጥራቸዉን አቅርበዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!