ቀን 4 / 3 / 2013 ዓ.ም

በትምህርት ቤቶች ለኮቪድ 19 በሽታ መከላከል  የሚውል የ1.5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለፀ፡፡

ኮርዲያድ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ደርጅት  ለተማሪዎች አገልግሎት  የሚውል  አንድ መቶ ሰማንያ ሺ  ለህጻናት እና 39 ሺ ለአዋቂ የአፍ እና አፍንጫ  መሸፈኛ ማስክ ፣ ዘጠና ስምንት  የሙቀት  መለኪያ  ማሽን እና ስድስት ሺ  ሳኒታይዘር ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልፅዋል፡፡ የቢሮው ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በቁሳቁስ ርክክቡ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው እንደገለፁት የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የብዙ አካላት ተሳትፎን በማካተት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው በዛሬው እለት ገብሬኤልዋ የህፃናትና ሴቶች በጎ አድራጎት ደርጅት አማካኝነት ኮርዲያድ በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለተደረገው  ድጋፍ  በትምህርት ቢሮ እና በተማሪዎች ስም አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡  

የገብሬኤልዋ የህፃናትና ሴቶች በጎ አድራጎት ደርጅት  ሀላፊ ቤዛ ሃይለማሪያም በበኩላቸው እንደገለፁት  ኮቪድ 19 ወረርሽኝ  በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ ለብዙ ሰዎች ህይወት  መጥፋትና ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለ  ወረርሽኝ ነው ብለዋል፡፡ ህይወትን ከማጥፋት በሻገር  የትምህርት ሂደትን  በማስተጓጎል በርካታ ተማሪዎች እቤት እንዲቀመጡ በማድረጉና አሁን የተጀመረውን  የመማር ማስተማር  ስራ ለማገዝ በአንድ ነጥብ አምስት ሚለዮን ብር ወጪ የሚገመት የአፍ እና አፍንጫ  መሸፈኛ ማስክ፣የሙቀት  መለኪያ  ማሽን እና ሳኒታይዘር  ድጋፍ መደረጉን  በመግለጽ በድርጅታቸዉ ጥያቄ መሰረት ኮርዲያድ ግብረ ሰናይ ደርጅት ድጋፉን በመስጠቱ  ድርጅቱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል ፡፡ አክለውም  ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ የመስራትና ለተማሪዎች የሚደረገው  ድጋፍ  ተጠናክሮ  ይቀጥላል ብለዋል፡፡

መረጃዎችን  በፍጥነት  ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና  የትዊተር  ገፃችንን  ሰብስክራይብ  ያድርጉ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

ባልታጠበ  እጅ  አይንዎን  አፍዎን  እና  አፍንጫዎን  ባለመንካት  በዙሪያዎ  ላሉ  ሰዎች  አርአያ  ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s