የ2013 የትምህርት ዘመን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀመር የነበረው የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡



ቀን 27 / 2 / 2013 ዓ.ም
 
የ2013 የትምህርት ዘመን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም  ይጀመር የነበረው የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት  ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡
 
ለክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ  የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የክለሳ ትምህርት ግን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
 
በአዲስ አበባ ከተማ የ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለኮቪድ-19  ወረርሽኝ በማያጋልጥ ሁኔታ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት  ስራዎች  በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡
 
ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጪ በተቀሩን ክፍሎች ትምህርት  ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አስፈላጊ ዝግጅቶች በተሟላ ደረጃ እስኪጠናቀቁ ድረስ በከተማዋ ለመጀመር የታቀደው  የገጽ ለገጽ  ትምህርት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 
ከባለፈው ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት የጀመረው  የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የገጽ ለገጽ የክለሳ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት  ግን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
 
መረጃዎችን  በፍጥነት  ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና  የትዊተር  ገፃችንን  ሰብስክራይብ  ያድርጉ!
 
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
 
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
 
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
 
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
 
ባልታጠበ  እጅ  አይንዎን  አፍዎን  እና  አፍንጫዎን  ባለመንካት  በዙሪያዎ  ላሉ  ሰዎች  አርአያ  ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s