የሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅም በምንወስደው የምግብ አይነት ይወሰናል::
አብዛኛውን ጊዜ እጃችንን እንድንጣጠብ እና ማህበራዊ እርቀታችንን እንድንጠብቅ ይነገረናል::ነገር ግን ከዚህ ሌላ እራሳችንን ከየትኛውም በሽታ ልንከላከል የምንችልበት ሌላኛው አስፈላጊ ነገር የአመጋገብ ስርዓታችን ነው::
ለኮሮና ብቻ ለይተን የምንመገበው የምግብ አይነት ባይኖርም ንጹህ እና ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት ሊኖረን ይገባል::
የሰውነት የበሽታ የመከላከል አቅም የሚጨምሩ የምግብ አይነቶችን ለምሳሌ፦ቲማቲም፣ ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል፣ ለውዝ ፣አሳ ዘይት የመሳሰሉትን የምግብ አይነቶች በአብዛኛው በሰውነታችን ለሚፈጠረው የህዋስ መቆጣት(Inflammation) የመከላከል አቅም አላቸው::
በተለይም ቫይታሚን ሲ እና ዚንክ የበሽታ መቋቋም ስርዓትን(immune system) በትክክል እንዲሰራ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ናቸው::
እንደ ብርቱካን፣ ሎሚ ፣ፓፓያ ፣ማንጎ፣ አናናስ፣ አፕል በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ፍራፍሬዎች ናቸው::
እንዲሁም ውሃን አዘውትሮ መጠጣት ለጤና እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡
በአጠቃላይ ያልበሰሉ(ጥሬ ስጋ) እና እሳት ያልነካቸው ምግቦችን አለመጠቀም እና አልኮል መጠጥን ማስወገድ መመገብ ወይም መጠጣት ከሌለብን ነገሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ::
መልካም የጤና ቀን ይሁንላችሁ !
ምንጭ፡- ዶ/ር ሃይለልዑል መኮንን
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
“የነገ ህመምና ሞትን በዛሬ ጥንቃቄ እንታደግ!”