ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5798 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ስልሳ ዘጠኝ (169) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ35 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ ህይወት አልፏል። ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ሁለት (12) ሰዎች (10 ከአማራ ክልል እና 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 262 ነው።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡