እናመሰግናለን! አብዝቶ ይስጥልን !
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ለታላቁ የኢትዩጵያ የህዳሴ ግድብ የ 200,000 ሺህ ብር ቦንድ ግዥ የፈጸመ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ለተቋቋመዉ ሶሻል ትረስት ፈንድ ከየክፍለ ከተማዉ መምህራን ማህበሮች እንዲሁም ከማዕከሉ የማህበሩ ጽ/ቤት የተሰበሰበዉን 335,000 ብር ድጋፍ ለከተማዉ አስተዳደር አሰረክባል ፡፡
በተያያዘ ዜናም ማህበሩን እራሱን ለማስቻል በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ውስጥ የራሱ የሆነ ሁለገብ ማዕከል እና የመምህራን እጠቃላይ ሆስፒታል ለማስራት የኮንትራክተር ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማክስኞ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ተጫራቾችን ጋብዛል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡