ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 250 ነው።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡