እናመሰግናለን ! አብዝቶ ይስጥልን !
ት/ቤቶች ማህበራዊ ኃላፊነታቸዉን ከመወጣት አንፃር አርአያነት ያለው ተግባር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፈለ ከተማ አባይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሚገኙ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ለ 65 በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የተማሪ ወላጆች በጥሬ ገንዘብ ፣ የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በድጋፉ ወቅት የተገኙት የክፍለ ከተማችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ካሳሁን የትምህርት ተቋማትና ሰራተኞች እያደረጉት ያለው መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። አቶ ፍቃዱ አክለውም የመጣብንን የተፈጥሮ አደጋ ለመከላከል ሁሉም በያለበት ሊረባረብ ይገባል ። ይህ ክፉ ቀን ያልፋል ሁላችንም ካለን እናካፍል መምህራን የሁላችንም አርያ ናችሁ በርቱ እንበረታለን ሲሉ በአስተዳደሩ ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ።
በዚሁ ከፍለ ከተማ በወረዳ 05 እና 02 አስተዳደር ስር የሚገኙት ዴስትኒ አካዳሚ እና የኔታ አካዳሚ ገቢያቸው አነስተኛ ተብለው ለተለዩ 180 አባወራዎችና እማወራዎች ከ 180 ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና የተለያዪ ምግቦችን የክፍለ ከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Facebook : https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication እንራራቅ፣ እንታጠብ እንዲሁም አንጨባበጥ፡፡