በ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር በአጭር የፅሁፍ መልእክት ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ፣ በኤፍ ኤም 94.7 ሬዲዮና በሌሎች የኢንተርኔት አማራጮች ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እየተሰጠ ባለው ትምህርት በተለይም ድግሞ በትምህርት በቤቴ መርሃ ግብር ላይ የተማሪዎችን ተሳትፎ ለማጠናከርና በትምህርታቸው እውቀት መገብየታቸውን ለመለካት ሲካሄድ በነበረዉ የ8455 የሽልማት መወዳደሪያ መልዕክት መላኪያ ላይ የአሸናፊ ተማሪዎች ሽልማት መርሃ ግብር ዛሬ ግንቦት 13/2012 ዓ/ም ተካሄደ፡፡ 

በተካሄደው መርሃ ግብር ከ7ኛ –12ኛ ክፍል ላሉ 30 አሸናፊ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ላፕ ቶፕ ኮምፒውተር እና ለ11 ልጆቻቸዉን ለዚህ ላበቁ ቤተሰቦች የ43 ኢንች ቴሌቪዥን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

በሽልማት መርሃ ግብሩ ተገኝተው ሽልማቱን ያስጀመሩትና መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ (ኢ/ር) ታከለ ኡማ እንደገለፁት አዲስ አበባን ከሚመጥን ተግባር  መካከል  ትውልድን በትምህርት መገንባትና ተገቢውን ተግባር በመፈፀም በትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ልዩነት በማስተካከል  በመንግስት ትምህርት ቤት መማር ኩራት መሆኑን በስራ ማሳየት ነው ብለዋል፡፡  አክለውም ለዚህ ደግሞ በተማሪዎችና በመምህራን ላይ ኢንቨስትመንት በመጨመር በተማሪዎች አልባሳት( ዩኒፎርም ) ፣ በምገባ መርሃ ግብር ፣ በትምህርት መማሪያ ግብአቶች እና መስል የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በአዲስ መልክና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡ በተያዘው አመት ለ300ሺህ ተማሪዎች እየተደረገ ያለው “የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር” በቀጣዩ አመት 600 ሺህ ተማሪዎች የሚካተቱበት ይሆናል ሲሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ ጨምረዉ ተናግረዋል።

የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም  ሙላቱ የትምህርት መርሃ ግብሩ እንዲሳካ ከፍተኛ  አስተዋጽኦ ላደረጉ የከተማው  አስተዳደር ፣ በየደረጃው ላሉ የትምህርት ቢሮ አመራሮችና የትምህርት ባለሙያዎች፣ ለአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለሌሎች በትምህርት ቢሮ ስም አመሰግናለሁ  ብለዋል፡፡

One thought on “በ”ትምህርት በቤቴ“ መርሃ ግብር በአጭር የፅሁፍ መልእክት ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s