ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ አፈጻጸም በትምህርት መሻሻል መርሃግብርና በተማሪዎች ፈተና

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተማችን ባለፉት 5 አመታት የተለያዩ ተግባራት ስታከናውን ቆይታለች፡፡ የትምህርት ጥራት ፓኬጅ ስድስት ፕሮግራሞች ሰተገብር የቆየ ሲሆን በትምህርት መሻሻል በርሃግብርና በተማሪዎች ፈተና ዙሪያ  አፈጻጸሙ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የትምህርት ቤት መሻሻል በርሀ ግብር

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው ጥራት ያለው ትምህርት የማዳረስ ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የትምህርት መዋቅሩ አስተማማኝ መልካም አጋጣሚ እንዳሉት ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ባሁኑ ግዜ በተጠናከረ ሁኔታ ተደራጅቶ የገባው የወላጅ ተማሪ መምህር ህብረት (ወተመህ) መውሰድ ይቻላል፡፡ ትምህርት ቤቶች በስታንዳርዱ መሰረት በማደራጀት ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ያሉበት ደረጃ በግምገማ ተለይቶ ደረጃ እየተሰጣቸው የማስኬድ አግባብ ላይ ተደርሷል፡፡

ይሁን እንጂ ባሁኑ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ የሚያሳዩትን ፍላጎት አውን ለማድረግ በትምህርት ስራው ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ የተለያዩ የንቅናቄ መድረኮችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡በመሆኑም የኀብረተሰቡ ተሳትፎና አጋርነት ታክሎበት ህዝቡ ለትምህርት ስራ ያለውን ባለቤትነት የበለጠ በማጠናከር የፋይናንስና የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ፣ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት፣ነባሮቹንም በማደስ፣ የትምህርት ግብአቶችን በሟሟላት ረገድ ተገቢውን ተሳትፎ በማድረግ አጋርነቱንና ባለቤትነቱን አንዲያረጋግጥ ማስቻል ተገቢ ነው፡፡

ት/ቤቶች ተፈላጊውን የብቃት ደረጃ ማሟላታቸውን በመገምገም ብቃታቸው የተረጋገጠላቸው ብቻ ዕውቅናና ዕድሳት እያገኙ የሚሰሩበት ህጋዊነት ያለው ሥርአት በመዘርጋት በተቋማት መካከል መልካም የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር ከማድረግ አንፃር በከተማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ደረጃ ምደባና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን በጥራት የመምረጥና ዕውቅና የመስጠት፣ከተፈላጊው ደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ክፍተታቸውን በማሳየት በቀጣይ ወደ ተሻለ ደረጃ መድረስ እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተፈላጊ ግብ የሆነውን የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር እንዲያሻሽሉ የማድረግ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል::

በ2006 ዓ.ም በተደረገው የ20% የውጭ ኢንስፔክሽን ትግበራ በተደረገው መሠረት በከተማችን የሚገኙ 243 የመንግስትና የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ 39 (21%) የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች እና 13(23%) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ ሶስት ወይንም ደረጃውን ያሟሉ ሲሆኑ፣127(68%) የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች እና 37 (66%) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በደረጃ ሁለት ላይ በመሆናቸው በመሻሻል ላይ የሚገኙ እንዲሁም 21(11%) የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤቶች እና 6(11%) የሁለተጃ ደረጃ ት/ቤቶች ደረጃ አንድ ማለትም ደረጃውን ያሟሉ ናቸው፡፡በሁለቱም የትምህርት ደረጃ እርከን ላይ ደረጃ 4 ሆኖ ደረጃውን በከፍተኛ ደረጃ ያሟላ ተቋም የሌለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ከዚህ አንፃር በደረጃ አንድና ሁለት የሚገኙ የትምህርት ቤቶቻችን መብዛትና በደረጃ 4 ላይ የተፈረጀ ትምህርት ቤት አለመኖር ትምህርት ቤቶቻችን ስታንዳርዱ ጠብቀው እንዲደራጁ ማድረግ ላይ ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ያሳያል፡፡

የተማሪዎች ውጤት

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ ግብር ተቀይሶ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ፡፡ የመርሃ ግብሩ ዋና አላማ የተማሪዎችን ውጤትና አስተሳሰብ ማሻሻል ነው፡፡መርሃ ግብሩን ተግባራዊ በማድረግ በመጀመርያ ደረጃ የክህሎት መሻሻል ማሳየት ጀምሯል፡፡

በ10 ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት የአዲስ አበባ 2.00 ነጥብና በላይ በመቶኛ

4

 

ከመረጃው መረዳት እንደሚቻለው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና(10ኛ ክፍል) ውጤት ወጣ ገባነት ያለው ነው፡፡ ውጤቱም በተከታታይ አመታት ሴቶች ከወንዶች ብልጫ ያላቸው ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከሃገር አቀፍ ጋር ሲነጻጸር አበረታች ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ከ10ኛ ክፍል ወደ መሰናዶ ያለፉ (ከ 2003-2006 ዓ.ም)

5

የ2ኛ ደረጃ የመጀመርያው ሳይክል ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ካለፉ የወደፊት ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው የሚያመቻቹበት እና መሰረት የሚጥሉበት በመሆኑ ከ2003 ዓ.ም ከነበረው 58.9% በ 2006 ዓ.ም ወደ 66.84% በ 7.7% የጨመረ መሆኑን ያሳያል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተና 50% (350 እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ከ2003-2006 ዓ.ም)

6

የ2ኛ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን የሚገቡበት እንደመሆኑ መጠን ከ2003 ዓ.ም ከነበረበት 40.2% በ 2006 ዓ.ም ወደ 40.16% በ 0.04 የቀነሰ መሆኑን ያሳያል፡፡ በጾታ ደረጃ ስናየው ላለፉት 4 ተከታታይ የትምህርት አመታት ወንዶች ከሴቶች የበለጡ እንደሆኑ ነው፡፡

የክልላዊ ፈተናን በተመለከተ

ከ8ኛ ክፍለ ወደ 9ኛ ክፍ የተዛወሩ ተማሪዎች ብዛት (ከ 2003-2006 ዓ.ም)

7

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ 2003 ዓ.ም ከነበረበት 72.0% በ2006 ዓ.ም ወደ 67.6% በ 4.4% ዝቅ ብሏል፡፡ በሴት እና በወንድ ተማሪዎች መካከል ስንመለከት ሴቶች ከወንዶች በተሸለ ደረጃ ወደ 9ኛ ክፍል የተሸጋገሩ ሲሆን በ 2003 ዓ.ም ከነበረው 4.4% የሴቶች ብልጫ በ 2006 ዓ.ም ወደ 6% ከፍ ብሏል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s